ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ያዘጋጀው የ 2025 ቀጠናዊ የፍልሰተኞች ምላሽ እቅድ በበይነ መረብ አማካኝነት ይፋፕሮጀክቱ በዋናነት ፍልሰተኞች ከኢትዮጵያ ወደ ሌሎች ሀገሮች፣ ከሌሎች ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ በኩል ዝውውር ሲያደርጉ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ህጋዊ እንዲሆኑ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ነው። መንግስት መደበኛ የሰዎቸ ፍልሰት አስተዳደር እንዲኖር ከመዳረሻ ሀገራት ጋር ስምምነት ማድረግ፣ ተጋላጭ የሆኑ ስደተኞችን መደገፍ፣ ወደ አገራቸው የመመለስና የመቀላቀል ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ።
ኢ- መደበኛ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ ዝውውር እንዲኖር ለማድረግ የመንግስት ጥረት ብቻውን በቂ አይደለም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ለጋሾች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የልማት አጋሮች ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት፣ ከዓለም አቀፍ አጋሮች እና ከልማት ድርጅቶች ጋር በመሆን ፍልሰት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ሥርዓት ያለው እና ለሁሉም የሚጠቅም መሆኑን ለማረጋገጥ የበኩሏን ሚና ለመጫወት ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል።