A Message from the Head of the Tigray Youth Affairs Bureau

የትግራይ ወጣቶች ቢሮ ሐላፊ መልእክት
ወጣት የኣንድ አገር የማይተካ የለውጢ ሐይሊ እንደሆነ ግልፅ ነው። ወጣትነት ኣካላዊና ኣእምሯዊ እድገት ጎልቶ የሚታይበት፣ መመራመር እና ፈጠራ ስራ የምጀመርበት፣ ለቀጣይ ህይወት ዘመኑ መሰረት የሆነው ስብእናና መንነት የሚበለፀግበት ወሳኝ የዕድሜ ደረጃ ነው። የትግራይ ወጣቶች ቢሮም ይህንን ወሳኝ እምቅ የለውጢ ሐይሊ መገንባት ኣገር መገንባት ነው ብለን ቱክረት ሰጠን እየሰራን እንገኛለን። ሆኖም በትግራይ ውስጥ ባጋጠመው ኣውዳሚ ጦርነት ምክንያት ወጣቱ በኣካል፣ በስነ ኣእምሮ ፣ በኢኮኖሚና ማሕበራዊ ስለተጎዳ ተስፋ በመቁረጥ እግሩ ወደ መራበት እየፈለሰ ነው፣ በተለያየ ኣደንዛዥ ዕፆች ሱስ እየተጠመደ ይገኛል፣ ወላጆቹን ማዋረድ፣ መግደል፣ ሴቶችን ባለተለመደ ሁኔታ መድፈርና በግፍ መግደል የመሳሰሉ ኣደገኛ የሆነ የባህሪ ለውጥም እየታየበት ይገኛል ። በተጨማሪም ስራ ኣጥነት፣ ብድር ኣለማግኘት፣ መስሪያና መሸጫ፣ መኖሪያ፣ ስልጠና፣ የመልካም ኣስተዳደር እጦት ወዘተ ለወጣቶች ተስፋ እያስቆረጠ ይገኛሉ። በሌላ በኩል በገጠመው ተግዳሮት ተስፋ ሳይቆርጥ ነገ የተሻለ ቀን ይሆናል በምል ተስፋ በኣካባቢው የሚገኝ ሃፍተ ገነት ተጠቅመው በኣጭር ግዘ ውስጥ ከፍተኛ ለውጢ ያስመዘገቡ ወጣቶች ኣሎ።
ስለሆነም የትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የትግራይ ወጣቶች ከገጠመው ፈተና ተላቆ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያግዚ ዕቅድና ፕሮግራሞችን ነድፎ ከባለድርሻ ኣካላት ጋር በመተባበር በትጋት እየሰራን እንገኛለን። ቢዚህ መሰረት ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ከ311 ሚሊየን በላይ ቋሚ እና ግዚያዊ ስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፤ ከ1.1 ሚሊየን በላይ የሚሀኑ ወጣቶች የግንዛቤ ማስፋት ስልጠና ተሳትፏል፣ ከ1.16ሚሊየን በላይ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ ኣገልግሎት ተሳትፎ ከ1.67 ሚሊየን የሕብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድግ ተችሏል።
ይህ የተወሳሰበ የወጣቶች ችግር በተለመደው ኣዃሃን መፍታት በቅ ለማይሆን ሁሉንም ያሳተፈ ግልፅነትና ተጠያቅነት ያለው ‘ የወጣትች እድገት ፍኖተ ካርታ Youth Development road map’ ተቀርፅ ከላይ እስከ ታች የባለድርሻ ኣካላት የተቀናጀና የተናበበ ኣሰራር ስለሚያስፈልግ የመተባበር ፕላትፎርም (Coordination Mechanism ) እያዘጋጀን እንገኛል።
ስለሆነም ሁሉም ባለድርሻ ኣካላት ለወጣቶች ቱክረት ኣድርግ ዕቅድ ውስጥ ኣካቶ እንዲሰሩ፣ ወላጆች እና ዩማሕበሱ ደሞ የቻለውን ሁሉ እንዲተባበር እና ከጥፋ እንዲታደጋቸው፤ ሙሁራትራን የዲያስፎራ ወንድም እህቶች ድርሻቸው እንዲወጡ፣ ወጣቶች ራሳቸው በሁሉም ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያችን እናስተላሊፋለን